ኢትዮጵያን ሯጮች በሳውዲ የደገሙት የአረንጓዴው ጎርፍ ድል (ክፍል 9)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ከሰሞኑ ሰበር ቅኝት ...

ወደ እኛ ዘመን የተስፋ ምድር ወደሆኑት ዐረብ ሀገራት በተለይም ወደ ሳውዲ ዐረቢያ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሚያደርጉት ጉዞና በሚያጋጥማቸው መከራ ዙሪያ በተከታታይ ክፍሎች የማደርገውን ቅኝት አላቆምኩም። ያለፈውን በትዝታ የማስቃኘው ዝካሬየ ነገም ይቀጥላል ... የዛሬው ቅኝቴ ከዚህ በፊት እንደማደርገው በሰሞነኛው ትኩረቴ በጅዳው ማራቶን በኢትዮጵያን አትሌቶች በተገኘው ድል ዙሪያ በማተኮር ያየሁ የሰማሁትን ከመረጃ ጋር ላጋራችሁ ግድ ይለኛልና ፈቃዳችሁ ከሆነ ተከተሉኝ ...

ተንቀሳሳሽ ስልኬ ደጋግማ ትጮሃለች ... የተደወለልኝ ገጽታችን በስፖርት እንቀይር በሚል በዐረብ ሀገራቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደግ የማይነሳ ስማችን ለመቀየር በሚደረግ የስፖርት እንቅስቃሴ ታች አምና የተዋወቅኩት ወጣት ነበር። ስማችንና ገጽታችን እንቀይር ብለው የተነሱት ወጣቶችን ዙሪያ አንድ ዘገባ ሰርቸ ነበር። ሁኔታውን ጠጋ ብሎ ለተመለከተው ሃቅ አለው! አሁን አሁን በጥቂት ምግባረ ብልሹ ዜጎች በሚፈጸም ምግባር የብዙዎቻችን ስም በጥሩ አይነሳም። ገጽ ስማችንን ለመቀየር ደግሞ ስፖርት ለጊዜው የተገኘው ብቸኛ አማራጭ በመሆኑን አጥብቀው ከሚያምኑት መካከል ይህ ወዳጀና ጓዋደኞቹ ዛሬ በጅዳ የሚደረገው ማራቶን የኢትዮጵያን አትሌቶች ተሳታፊ መሆን ልዩ ስሜት እንደሚሰጠው አያስቸግርም።

ስልክ የደወለለኝ ወዳጀ የሚሰራበት ኩባንያ የጅዳ ማራቶን ስፖንሰር ካደረጉት ኩባንያዎች መካከል አንዱ በመሆኑ፤ አንዳንድ መረጃዎችን ከሳምንት ጀምሮ ያቀብለኝ ነበርና የስልኩን ጥሪ እንደሰማሁ በማራቶኑ ዙሪያ ሊያነጋግረኝ እንደሆነ አልጠፋኝም። የሚንጫረረውን ስልክ ከማንሳቴ አስቀድሞ ፈጥኘ የተመለከትኩት የቀን መቁጠሪያየን ነበርና የስልኩን ጥሪ መልዕክት ለመገመት አልተቸገርኩም። በአስገራሚ ፍጥነት ስለሚጓዘው ጊዜ ለማሰላሰልም ሆነ የጀመርኩትን ስራ ለመጨረስ ጊዜ አልወሰድኩም። ስልኩን አንስቸ ወዳጀን አነጋገርኩት ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ