መስፍን ማሞ (ሲድኒ-አውስትራሊያ)

ለቀደሙት የተባለውን ሰምታችዃል……… ይህም ተፅፏልና!

ለምትበልጠው ፀጋ ቅኑ። እኔም ዳግመኛ እጅግ የበለጠ ሌላ ጎዳና አሳያችዃለሁ፤ በሰዎች ሁሉ ቋንቋና በመላእክት ቋንቋ ብናገር፤ ትንቢትም ብናገር፤ የተሰወረውን ሁሉና የጥበብን ሥራ ሁሉ ባውቅ፤ ተራራም እስካፈልስ ድረስ ሃይማኖት ቢኖረኝ፤ ያለኝንም ሁሉ ለድሆች ባበላ፤ ዳግመኛም ሥጋዬን ለእሳት ቃጠሎ ብሰጥ፤ ፍቅር ከሌለኝ የተጠቀምሁት የለም። ፍቅር ያለው ሰው ሩህሩህ ትዕግስተኛም ነውና።

 

 

በፍቅር መልካም የሆነ (ፍፁም የሆነ) አይቀናም።ቸልም አይልም፤ አይታበይምም። የሚያሳፍር ነገርም አያመጣም።ለብቻው ተድላን አይሻም። አይበሳጭም። ክፉም አያስብም። በግፍ ዕደስ አይለውም። በዕውነት ግን ደስ ይለዋል። በሁሉ ይታገሳል። በሁሉም ይታመናል። ጸንተውም የሚኖሩ ሃይማኖት፤ ተስፋ፤ ፍቅር ናቸው። ከሁሉም ፍቅር

ይበልጣል። (1 ቆሮ፤ 12 31 13 1 – 13)

እናንት የተስፋይቱ ምድር የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ! እነሆ ሁሉም እንደ የእምነቱ አምላኩን እያመሰገነ ለምዕተ ዓመታት በሠላም የኖረባት ኢትዮጵያ ስለምን ልጆቿ በዚህ ዘመን በሃይማኖቶች ጣልቃ ገቦች ሳቢያ ጸንተው የኖሩ ሃይማኖቶች (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደግሞም እስልምና) አማኒዎቻቸውን ከፋፍለው ይታመሳሉ? ይጣላሉ? ይጠላላሉ? …………

ስለምንስ የተስፋይቱ ምድር ልጆች በዚህ ዘመን ፍፁም ተስፋ አጡ? ስለምንስ በለምለሚቷ  ገራቸው በምድረ በዳ እንደተጣለ ግዞተኛ ተስፋ የራቃቸው፤ ጨለማ የዋጣቸው ሊሆኑ ቻሉ? ……… ስለምንስ ከኢትዮጵያ ልጆች መኻል ፍቅር ራቀ? ስለምንስ በዚህ ዘመን የባንዲራ የ ገር የወገን ፍቅር ፤ ለጎጥ ለዘረኝነት ለክፍፍልና ለቂም በቀል ምርኮ አደረ? ስለምንስ ወንድም በወንድሙ፤ እህትም በእህቷ ላይ ተነሱ?

ስለምንስ አብናቶችና (አባት እናቶችና) ታሪክ ተዋረዱ? ሰማዕታት ተወገዙ? ስለምንስ ኢትዮጵያዊነት አሳፋሪ፤ ጎጠኝነት/ዘረኝነት አስከባሪ ሊሆን ቻለ? ……..

የተስፋይቱ ምድር የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ!............

ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ይቀይር ዘንድ ይቻለዋልን? (ኤር 13፤23)

እናንት የተስፋይቱ ምድር ልጆች ሆይ! የነብር መልኩ ዥንጉርጉርነቱ እንደሆነ፤ የኢትዮጵያዊነት መልኩ ዕምነት፤ ተስፋ፤ ፍቅር መሆናቸውን ትክዱ ዘንድ ይቻላችዃልን? እንግዲህስ ስለምን ኢትዮጵያዊነት መልካችሁን - ዕምነት፤ ተስፋ፤ ፍቅር - ሊያሳጧችሁ ለታበዩት የክፉ ዘመን ሰዎች  ሞታችሁ ፈሰሰ? ክንዳችሁስ ዛለ? ለቀደሙት እንደተነገረ ሰምታችዃል። እንዲህ ተፅፏልና!

ፍርድ ሞልቶባት የነበረ የታመነችይቱ ከተማ ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፤ አሁን ግን ገዳዮች አሉባት። ብርሽ ወደዝገት ተለወጠ። የወይን ጠጅሽ ከውሃ ጋር ተደባለቀ። አለቆችሽ አመፀኞችና የሌቦች ባልን ሮችሆኑ፤ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ።ዋጋም ለማግኘት ይሮጣሉ።ለድሃ አደጉ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም። (ኢሣ፤ምዕ. 1. 21 -23)

እነሆ በዚህ ዘመን ደግሞ ይህ ቃል በተስፋይቱ  ገር በኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ በተቀመጡ አመፀኞች ህወሃታውያን ገዢዎች እየተፈፀመ አይደለምን? እነሆስ በዚህች  ገር ላይ የግፍ ሽክናው ሞልቶ ይፈስ የለምን? እንግዲህስ ግፉ አይበቃምን?

ዕውነት ዕውነት እላችዃለሁ! ……ኢትዮጵያዊን /ሰውን/ በአምሳሌ ፈጥሬዋለሁና፤ የዕምነት የተስፋ የፍቅር መንበሬም ቅድስቲቱ ምድር ኢትዮጵያ ናትና…በህዝቤና በመንበሬ ላይ የአመፅ ሰይፋቸውን ላነሱ ሁሉ ወዮላቸው!! ወዮ! የተሸከመውን የግፍ ቀንበር ለመጣል ህዝቤ እጅ ለእጅ ተያይዞ የተነሳ ዕለት!........

ለቀደሙት እንደ ተነገረ፤ እናንተም የተስፋይቱ ምድር ልጆች እንግዲህ ስሙ!!

እንደየእምነቶቻችሁ ፀንታችሁ፤ ዛሬን ለነገ ተስፋ ሰንቃችሁ፤ በዘርና በጎጥ ሳይሆን በፍቅር አንድ ህዝብ አንድ አካል አንድ ልብ ሆናችሁ፤ እነሆ ኢትዮጵያዊ መልካችሁን ሊያጠፉ በተነሱ የክፉ ዘመን ገዢዎቻችሁ ሁሉ ላይ ተነሱ! ታሸንፉማላችሁ!

እናንት የኢትዮጵያ ልጆች ኢትዮጵያውያን ሆይ! ዕውነት ዕውነት እላችዃለሁ፤ የእናንተና  ገራችሁ ህልውና፤

በዚህ ዘመን ከገደል አፋፍ ደርሷልና፤ እርዱኝ እረዳችዃለሁ!

እንግዲህስ የፈሰሰ  ሞታችሁ ይኾምጥጥ! የዛለ ክንዳችሁ ይነሳ! ያዘመመ ዕምነታችሁ ይቅና! ያቄመ ልባችሁ በፍቅር ይሙላ! የራቃችሁ ተስፋ ይቅረብ! ከፍቅርጠላትከጎጥዘርደዌትፈወሱዘንድ!!! ቃሌ ይህቺ ናትና!……. {እነሆ ንገር የተባልኩትን ተናግሬያለሁ።

ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይስማ!!}

(መስፍን ማሞ ተሰማ፤ ሲድኒ አውስትራሊያ፤ በ23ኛው የህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን ግንቦት

2006/2014 – This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)_

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ