“ወጣቱ አንበሳ ላገርህ ተነሳ...”
የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። እዲሱ አመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ብስራት ይዞ የሚመጣ ይሁን። ያለምንም ደም መፋሰስ ይህ ዘረኛ የወያኔ ገዢ ቡድን መቃብር ገብቶ፤ ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና በታኝነት ከምድራችን ጠፍቶ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ፤ ሲያጠፉ የሚቀጣቸውን የሚሽራቸውን፤ ሲያለሙ የሚሾማችውን የሚሸልማቸውን መሪዎች በድምጹ መርጦ፤ የሚኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘር ማንነቱ በፊት በኢትዮጵያ ሲምል ሲገዘት የምናይበት፤ ዜጎች ሁሉ ለሀገሬ፤..... ለወገኔ.. እያሉ ሲተጉ፤ ለጋራ እድገትና ብልጽግና ሲጓጉ....አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እያሉ አንዳቸው ላንዳቸው ሲሞቱ የምናይበት የተአምር ዘመን ይሁንልን,....ዘረኞች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚጠፉበት ዘመን ይሁንልን....2006. አሜን!
አርቲስቶች የተሰጥኦና የህዝብ ሁለንተናዊ ባህልና ወግ፤ እናም የህዝብ ድጋፍና አድናቆት ውጤቶች እንደ መሆናቸው፤ ስራዎቻቸው ሁሉ የህብረተሰብ ህይወት ነጸብራቆች የመሆን ተፈጥሮአዊ ግዴታ አለባቸው። ሰላምና ጦርነት፤ ድልና ሽትንፈት፤ ደስታና ሀዘን፤ ፍቅርና ጥላቻ ምን ጊዜም ከሰው ልጅ ጋር የሚኖሩ ክስተቶች በመሆናቸው፤ ሰውም በጥብበ ስራዎቹ ውስጥ እነዚህን ባህሪያት እያንጸባረቀ፤ ይማማርባቸዋል። ይዝናናባቸዋል። ያስተላልፋቸዋል። ለሚከታተል ትውልድ የታሪክ መንገሪያም ያደርጋቸዋል። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ ይህንን ይጫኑ!)



