ዘራፊ ሚሊየነሮች
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ውድ አንባቢያን ወደ ዋናው ጉዳይ ከመሄዴ በፊት ልጠቁም የምፈልገው ነገር የማቀርባቸውን ጽሁፎች በተመለከተ የምትጽፉልኝን አስተያየቶች፤ ትችቶችን አጠቃለው ሁሉንም በጥሞና አነባቸዋለሁ። እናም ሁላችሁንም ከልቤ ሳላመሰግን አላልፍም። ትችት ያስተምራል። የድጋፍም ሀሳብ ያስተምራልም ያበረታታልም። ሁለቱም እኩል ይጠቅማሉ። ወደፊት ከምትልኩልኝ መልሶች አለፍ አለፍ እያልኩ አጠር አጠር ያሉትን ሁለቱን ላንባቢያን አቅርቤ ወደምናገረው ነገር አልፋለሁ። ከዛሬ ልጀምርና “አያልቅበት .. “ ለሚለው ከደረሱኝ አስተያየቶች ሁለቱን ተመልከቱና ወደ አቅርቦቱ እንሂድ።
Nebrom Senay
አንተ እከካም ጥፍራም አንተም ወንድ ሆንክና ሴትን ትንቅ ጀመርክ? ማናባትህ ነው ያ ጭራቅ አባትህን \ደርግን\ የነፋው?
Was it not the valianr female fighters of the valian TPLF/EPRDF? You must be a super fool to expect any one going to the bush and die for you senile, aged old man. You shall perish without seing the comfort at 4 killo. You cannot even talk ina convincing manner. You re too old to covet power. chaw chaw
…..
Bizunesh Gizaw
Hi comrade Lulu Kebede
I appreciate your artilce. It reflects the everyday atrocities commited by the Weyane regime. This is not a state leadership but a mafia that empowers itself at any cost at the expense of dying peoples of Ethiopia simply to rob the country. As you said, they do not have any ethics. any morality or any element of leading a nation with a national interest. Even Fascist Benito Musolini and Adolf Hitler had national interest. These are so wild and greedy that they have no comparison except beasts.
Now the other problem is that there are over hundred active parties, some that seem to represent the same group of people, but most parties follow one trend; that is to serve the divisive scheme of Weyane. That means there are also greedy apostles that simply run for individual or narrow group power while we all know and the Ethiopian country man knows that unity is the only power to eliminate those vultures. For heaven sake let us advocate all Ethiopians, irrespective of race, language, religion and what have to stand in unison under one organization first to eradicate these vultures. If we agree to create a common forum of eradicating them, I assure you that the same forum can live side by side by respecting local rights, that means creating the basis of a federal form of administration or government!!!. We have to dream of an ideal unity devoid of personalities that we envison, that is out of cult. Then we may be able to see a democratic and developed nation. Could it be?
ለዛሬ ወደተነሳሁበት ጉዳይ እናልፋለን።
እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1983 ወያኔና ሻዕቢያ መላዋን ኢትዮጵያ ሲቆጣጠሩ፤ በየክፍለ ሀገሩ ከተሞች በገቡ ቁጥር የሕውሀት ሰራዊት ሁለተኛ ተግባር የነበረው ሁላችሁም አገር ቤት የነበራችሁ እንደምታስታውሱት፤ የመንግስትም፤ የህዝብም፤ የግለሰብም ንብረትና ሀብት እየዘረፉ፤ በሚያስገርም ፍጥነት ወደትግራይ ማሸሽ ነበር። በየባንኮቹ ይገኝ የነበረ የገንዘብና የወርቅ ክምችት፤ የሀብታም ግለሰቦች ትላልቅና ትናንሽ ተሽከርካሪዎች፤ የህዝብ ከሆኑ ነገሮች እሰከ ታች ቀበሌ ክበቦች ያለ ፍሪጅና ምግብ ማቅረቢያ ትሪ ሳይቀር፤ በፍጥነት እየዘረፉ በሚዘርፏቸው ካሚዎኖች እየጫኑ በፍጥነት ወደ ትግራይ እየወሰዱ መሸሸግ ነበር። ካሚዎኖች፤ ጀነሬተሮች፤ የእህል ወፍጮዎች፤ ቴሌቭዢኖች፤ ማናቸውም ዋጋ አላቸው ብለው የገመቱትን ቁሳቁስ ሁሉ፤ እንደ እብድ እየተክለፈለፉ ይሰበስቡ ያሻግሩ ነበር። በቀንም በጨለማም። ከጅማና ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የደን ሀብት ዘረፋ አልቀረም። የአዲስ አበባ ሕዝብ ቋሚ ምስክር ነው፤ ሁላችሁም ታውቃላችሁ። ያኔ ማታማታ የጎዳና ላይ መብራት እንዲጠፋ እየተደረገ፤ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተጎታቾቻቸው ምን እንደሆነ ሳይታወቅ እጅግ ብዙ ነገር ተጭነው በብዛት እየተከታተሉ ከከተማው ሲወጡ ማየት በየማታው የተለመደ ነበር።
ወራቶች እያለፉ ምንም የሚገታቸው ሀይል አለመኖሩንም አረጋግጠው ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረው አንደመረጋጋት ሲሰማቸው፤ ከሻዕቢያ ጋር እየተሻሙ ንብረትና ሀብት ዘረፋው ሳያቋርጥ፤ በተቆጣጠሩት ቴሌቭዢንና ራዲዮ፤ ማስታወቂያ ማውጣት ጀመሩ። ሰርቀው የሰበሰቡትን እቃ ሕዝቡ መልሶ የራሱን ንብረት እንዲገዛቸው ወተወቱ። ይህን በመሰለ ሁኔታ የሀገሪቱንና የህዝቡን ሀብትና ንብረት መቆጣጠር መዝረፍ ቀጠለ። ከውጭ የሚመጡ እርዳታዎችንም ወደካዝናቸው ማስገባቱን ቀጠሉ። ቤተ እስራኤሎችን የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ሲወስድ፡ ይከፈል የነበረውን 36 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ተቀብለው ወሰዱት። በወቅቱ በኢትዮጵያ የእስራኤል አንባሳደር የነበሩ ሰው ስማቸው ተዘንግቶኛል፤ ስለገንዘቡ ተጠይቀው አዲሱን መንግስት መጠየቅ እንደሚቻል ተናግረው ነበር።
ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት የሀገሪቱና የህዝብ የሆነ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በጃቸው አስገቡ።እቅዳቸው ያንን ገንዘብ በልዩ ልዩ ፈርጅ በመከፋፈል በሀገሪቱ ያለውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሙሉ በሞኖፖል ይዞ የሚያንቀሳቅስ ንብረትነቱ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ግንባር የሆነ በማእከላዊ ኮሚቴው የሚመራ ግዙፍ የኢኮኖሚ አውታር መፍጠር ነበር። በእርሻ፤ በኢንዱስትሪ፤ በትራንስፖርት፤ በግንባታ፤ በአገልግሎት ሰጭነት፤ በውጭና በውስጥ ንግድ፤ በማናቸውም መስክ መላ ሀገሪቱን የሚሸፍን የንግድ አውታር መመስረት ነበር።ነባሩን የንግድ ህብረተሰብ፤ ነባሩን ባለሀብት ቀስ በቀስ እያከሰሩና እያዳከሙ፤ የሚቀሙበትንም ዘዴ እየፈለጉ ሁሉንም ከጨዋታ ውጭ በማድረግ ጥቂት የትግራይ ባለሀብቶችን በመፍጠር፤ እነሱን የበላይ አድርጎ፤ ህዝቡን ጭሰኛ በማድረግ የአገዛዙን ቀጣይነት ማረጋገጥ አቋማቸው ነበር።
አነሆ በዚህም ራእይ መሰረት እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1987 ዓም አካባቢ በዘመቻ መልክ ስልሳ የሚሆኑ ትላልቅ የንግድ ኩባንያዎችና ድርጅቶች ከሶስት አስከ አራት ቢሊዮን በሚሆን የመነሻ ካፒታል ተቋቁመው ስራ ጀመሩ። ይህ ገንዘብ ስልጣኑን በተቆጣጠሩ አምስት አመት ውስጥ ከተዘረፈው ጥቂቱ ነበር። ከጥቂቱ በስተቀር የሁሉም ኩባንያዎች ዋና ጽህፈትቤቶች ማለት ይቻላል በመቀሌ ከተማ ሆኑ። የቦርድ አባላትና ሀላፊዎች የህውሀት ማእከላዊ ኮሚቴና ከፍተኛ አመራር አባላት ሆኑ።
ወያኔ ይህንን ኢኮኖሚውን በቁጥጥሩ ስር የማስገባት እንቅስቃሴ ሲያካሂድ፤ እንደሽፋን ያቀርቡት የነበረው ወሬ፤ ትግራይን መልሶ ለማቋቋም ወይም በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት መልሶ ማቋቋም የሚል ነበር። በመሰረቱ በጦርነቱ የተጎዳው መላው የኢትዮጵያ ህዝብና ሀገሪቱ እንጂ አንድ ክፍለ ሀገር ብቻ አልነበረም። ከሀገሪቱ በጀት ስልሳ ከመቶ የሚሆነው ለጦርነቱ ይውል ነበር። ያሁሉ ስንት ነገር ማልማት የሚችል ሀብት በነሱ ምክንያት ይባክን ነበር። እነሱ በሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች እየተረዱ ሲዋጉ፤ እኛ በጓዳ ማጀት ያለንን እያሟጠጥን እንታገል ነበር። በሁለቱም ወገን ያለቁት ተዋጊዎች የሀገሪቱ ልጆች ናቸው።
ሁለት ወንድማማቾች አንደኛው እርጉም ይሆንና፤ የጋራ ቤታቸውን አፈርሳለሁ ሲል፤ ሌላኛው ወንድም የለም አታፈርስም። መሰብሰቢያችንን አትንድም። እያለ ሲታገል፡ እርጉሙ በጠላት እየተረዳ እየታገዘ ሲታገል ይኸኛውም ወገን ቤት እንዳይፈርስ የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ፤ ጦርነቱ በእርጉማኑ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።ቤቱም ፈረሰ።እርጉሙ ወገን ቤቱን በማፍረስ አላቆመም። ወንድሞቹን ሁሉ አግልሎ፤ እነሱን ከፋፍሎ እያባላ፤ እንደጀመረው ከባእዳን ጋር ብቻ እየተወዳጀና እየመከረ የራሱን የበላይነትና ጥቅም መገንባቱን ቀጠለ።
እነዚህ ሰዎች ወታደሮም ናቸው። ነጋዴዎችም ናቸው። መንግስትም ናቸው። የሀገሪቱን ሀብትና ስልጣን ይዞ ለመዝለቅ ወታደራዊ እርምጃም ይጠቀማሉ። አስተዳደራዊ ስልጣንም ይጠቀማሉ። ሕግም ይፈጥራሉ ይጠቀማሉ። የመከላከያው፤ የደህንነቱ፤ የፖሊሱ ሀላፊዎች፤ ከየኩባንያዎቹ ከሚገኘው ትርፍ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተካፋይ በመሆናቸው፤ የአርባ፤የሐምሳ ሚሊዮን ብር ፎቅ እያስገነቡ በማከራየት ላይ ናቸው። አንድ የወታደር አዛዥ በምን መልኩ ነው የሀምሳ ሚሊዮን ፎቅ ገንብቶ ባለሀብት ሊሆን የሚችለው? ያውም ሀያ አመት ብቻ ያገለገለ፤ በተራ ሽምቅ ውጊያ የሰለጠነ፤አግባብነት ያለው የሚሊታሪ ኮሌጅ ተምሮ ሳይሆን እንዲሁ ኮሎኔል ጀነራል የሚል ስም የተለጠፈለት የመሀይም ሽፍታ ጥርቅም። በስርአቱ ላይ የሚነሳ የስልጣን ጥያቄ በቀጥታ በነዚህ ሰዎች ጥቅም ላይ የሚመጣ ስለሆነ አጥብቀው ህዝቡን ሊወጉት ይችላሉ። ከሀያ አመት በፊት የረባ ጫማና ልብስ አንኳ ያልነበራቸው ዛሬ ቢሊየነሮች ናቸው። ከየት አመጡ? ማንም የሚመልሰው አጭር መልስ ኢትዮጵያን ዘረፏት ነው። ህዝቡን ዘረፉት ነው። ከታች ያለው ሰፊ የህዝብ ልጅ፤ ወታደሩ መሳሪያውን በነሱ ላይ ካዞረ ነገሩን ሁሉ ሊያቀለው ይችላል። በነሱ መነዳቱ ከቀጠለ የህዝቡን ትግል ሊያከብደው ይችላል።
ኢኮኖሚውና ፖለቲካው እንግዲህ አሁን በጥቂት የትግራይ ታጋዮች የበላይነት ስር ወድቋል። ነባር ሀብታሞች አፈር ልሰው የተነሱ ታታሪ ኢትዮጵያውያን፤ ትግሬ ያልሆኑ ዜጎች ከጨዋታ ውጭ እየተደረጉ በሀያ አመት ውስጥ ከሰማይ ዱብ ያሉ ቢሊየነሮች እየተኳቸው ይገኛሉ። ከንግዲህ ጊዜውም ሀድራውም በቁጥር መቶም ይሁኑ ሁለት መቶ የወያኔ መሪዎች ይሆናል ማለት ነው።
በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ውስጥ የጉራጌ ባለሀብት አይኖርም።የአማራ የኦሮሞ የሌላውም ሁሉ ባለሀብት አይኖርም። በኢትዮጵያ ውስጥ በአፍሪካ ምናልባትም ብቸኛ የሆነ የድሀ አገር ሞኖፖሊ ካፒታሊዝም ይፈጠራል። እነዚያም ጥቂት ታጋይ የነበሩ ትግራይ ሰዎች ይሆናሉ። የቀረው ህዝብ የነሱ ሰራተኛና ጭሰኛ ይሆናል ማለት ነው።
በትግል ወቅት ከባዱን ስራ የሚሰሩት ጀግኖች ይሞታሉ። ፈሪዎቹ፤ አፈጮሌዎቹ፤ ሸፍጠኞቹና አስመሳዮቹ፤ የዋሆቹንና ጀግኖቹን እያስቀደሙ፤ እያገፋፈጡ አነሱ ይድናሉ። ሗላ ላይ የመስዋእትነቱ ፍሬ ቀማሽም ይሆናሉ። የድሉ ባለቤትም ይሆናሉ።
መለስ ዜናዊ የአድዋ ከተማን ባንክ እንዲዘርፍ ድርጅቱ ተልኮ ሰቶት፤ ጦር እየመራ አድዋ ከተማ በምሽት ከገባ በሗላ፡ የመጀመሪያዋ መትረየስ ስትተኮስ ሰራዊቱን ጥሎ የጠፋ የሸሸ ነበር። ቁጥራቸው በቀላል ለማይገመት ታጋዮች ማለቅ ምክንያት በመሆኑ፤ ታጋዮቹ መገደል እንዳለበት ወስነው፤ በእንዴት ያለ ሻጥር በወቅቱ ሳይገዳል እንደቀረ፤ ዛሬ በስደት ያሉ የትግል አጋሮቹ ያስረዳሉ። የነዚያ ጀግኖች ደም ያስገኘው ጥቅም ባለቤት ግን እሱና የፖለቲካውን ቁማር ይጫወቱ የነበሩ ባልደረቦቹ ሆነ።
በጀግንነት ደማቸውን አፍሰው እነዚህን ጥቂት የቀን ጅቦች ለድል ያበቋቸው የትግራይ አርሶ አደር ልጆች፤ ለኢትዮጵያ ሰላምና ዲሞክራሲ ታመጣላችሁ ተብለው ተዋጉ እንጂ ጥቂቱን የሕውሀት መሪዎች በቢሊየን ብር ለማንበሽበሽና ለማደለብ አልነበረም በረሀ የገቡት።
አራት ልጅ፤ አምስት ልጅ፤ እያፈኑና በፕሮፓጋንዳ እያታለሉ በጦርነቱ ያስፈጁባት ድሀ የትግራይ እናት፤ ድሀ የትግራይ አባት፤ ድሀ የትግራይ አርሶ አደር፤ ምናልባትም ሁሉም በልጆቻቸው ሀዘን ተጠብሰው አልቀዋል። ሞተዋል። ቢኖሩም እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ተጨብጠው የመከራ ህይወት በመግፋት ላይ ናቸው። አንዳቸውም ግን በልጆቻቸው ደም በተገኘው ድል ተዘርፎ የተቋቋመው ኩባንያ ሼር ሆልደር አይደሉም። ምናልባት በያመቱ ማዳበሪያ ካልወሰዳችሁ እየተባሉ በደከመ ጉልበት ያዘመሯትን ያመት ቀለብ የተበደራችሁትን ማዳበሪያ ክፈሉ አየተባሉ ያችኑ ከድብኝት እያራገፉ እየሸጡ ሚሊየነሮቹን በማደለብ ላይ ናቸው። ልጆቻቸውን የገበሩት አልበቃ ብሎ።
ከማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ የበለጠ የመከራ ገፈት እየቀመሰ ያለውን የትግራይ ህዝብ፤ የትግራይ አርሶ አደር፤ ከነዚህ ማፊያ ሰዎች ጋር እንዳታገናኙት። እነዚህ ማጅራት መችዎች የትግራይ ህዝብ ጀርባ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው፤ እየዋሹትና እያታለሉትም እያስገደዱትም ለዚህ እንዳበቃቸው፤ አሁንም ለሚነሳባቸው ሁሉ ያንን መከረኛ ደራሽ የሌለው ህዝብ እያገፋፈጡ፤ የሌብነት እድሜያቸውን ማስረዘም ስለሚፈልጉ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መጀመሪያ የትግራይን ሀዝብ ነው ማዳን ያለበት። የነጻነቱ ትግል መጀመር ያለበት የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ነው።
በዓጼ ሀይለስላሴ ዘመን ጉልተኞችና የመሬት ባላባቶች አርሶ አደሩ ለሚያርሳት መሬት ዋጋ በየአመቱ ያዘመረውን ወቅት እየጠበቁ የጎተራ የድብኝቱን እያሟጠጡ ብግር ብለው ይወስዱበት ነበር። ያለውን የቁም ከብት እየሸጠ እንዲከፍላቸው ያስገድዱት ነበር።ይህ በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ከፊውዳሉ ዘመን በከፋ መልኩ እየተካሄደ ያለ ግፍ ነው። የኢትጵያ አርሶ አደር የጥቂት ወያኔ ድርጅቶች የሀብት ምንጭ እየተደረገ ያለበት አሰራር ተፈጥሯል።
የህውሀት ኩባንያዎች ከውጭ የሚያስገቧቸውን ሸቀጦች ሸጠው ማትረፍ እንዳለባቸው ስልሚያምኑ፤ በግድ ህዝቡ ላይ ማራገፍና መገላገል አለባቸው። ማዳበሪያን ብንመለከት የሚታረሰው አካባቢ የቱንም ያህል ለም ቢሆን፤ የመሬቱ በኬሚካል ላይ ጥገኛ መሆን ወይም የገበሬው ገንዘቡን መቆጠብ የነሱ ጉዳይ አይደለም። ገበሬ ፈቀደም አልፈቀደ ማዳበሪያው ከውጭ የገባው እስከሚአልቅ ይታደላል።የአዝመራ ወቅት ሲደርስ ምን አዘመርክ? ስንት ቤተሰብ ትመግባለህ? አይደለም ጥያቄቄው። “ስንት ነው ያለብህ እዳ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ አንድታደርግ” ነው የሚባለው።
አሁን ባገራችን ያለው የሀብት ክምችት ሚዛን በንጉሱ ዘመን ከነበረው ሁኔታ ጋር ይመሳለላል። በዚያን ዘመን መሬትና በርካታ የንግድ ኩባንያዎች በመኳንንቱና በመሳፍንቱ እጅ የተካማቹ ነበሩ። መሬትን ብንወስድ በንጉሱ ቤተሰቦችና መሳፍንት መኳንንት እንዲሁም አንዳንድ ታማኝ ከፍተኛ የጦር አለቆች ንብረትና ሀብት ነበር። ያኔ አርሶ አደሩ የኔ የሚለው መሬት ነበረው ወይ? የለውም። አሁን የኢትዮጵያ አርሶ አደር የኔ የሚለው መሬት አለው ወይ? የለውም ።ዛሬ መሬቱን የተቆጣጠሩት የትግራይ ታጋዮች ቅድመ አብዮት መሬት ላራሹ ብለው አልጮሁም ነበር ወይ? ጮኸዋል። ታዲያ ዛሬ መሬቱን ተቆጣጥረዋል፤ ለምን መሬትን ላራሹ አላደረጉም? ለምን አርሶ አዱን ሰሰቱበት? ያ የሞተው መሪያቸው ይል እንደነበረው የአማራው ባለሀብት እንደገና መሬቱን አንዳይቆጣጠረው ሰግተው ነው? መሬት የመንግስት ነው። መንግስት ህውሀት ነው። እና ብለው የመንግስትና የብሄር ብሔረሰቦች ነው።አፍጦ አግጦ የምናየው እውነታ ግን መሬት የህውሀትና የውጭ የንግድ ሽርካዎቻቸው ነው። የኢትየጵያ አርሶአደር ዘለአለማዊ ጭሰኛ ነው።
የኢትዮጵያ አርሶ አደር ተደራጅቶ አምጾ መሬቱንና መብቱን ነጻነቱን ከነዚህ የቀን ጅቦች ካልነጠቀ፤ ጥቂት የህውሀት አመራር ባለሀብቶችን እያደለበ እርሱ እስከዘላለም በባርነት መኖሩ አይቀሬ ነው።
አቶ አስገደ ገብረስላሴ ወልደሚካኤል በትግራይ ውስጥ እየተዘዋወሩ የአርሶ አደሩን ሰቆቃ ሲያጠኑ፤ በኢትዮሚዲያ ድረገጽ ላይ ያወጡት ጽሁፍ በዋቢነት ሲጠቀስ፤ አርሶ አደሮች በብዛት የጋማና የቀንድ ከብቶቻቸውን ወደ ገበያ ሲነዱ አይተው፤ ገበያተኛውን አነጋግረው፤ ያገኙት መልስ “….እኛ ባሁኑ ጊዜ በአንድ በኩል የደደቢት ብድርና ቁጠባ፤ በሌላ በኩል የፓኬጅ፤ በተጨማሪ የማዳበሪያ ግዢ ብድር ክፈሉ፤ ካለበለዚያ ንብረታችሁና ሰብላችሁ ይወረሳል ስለተባለ ተደናገጥን። በአሁኑ ጊዜ የትግራይ አርሶ አደርና አነስተኛ ነጋዴ፤ ከአምስት አመት በላይ ውዝፍ እዳ አለበት…..” ብለው አርሶ አደሮቹ ነግረዋቸዋል።
አቶ አስገደ በዚያው ጽሁፋቸው ላይ ወረድ ብለው እያንዳንዳቸው ሀያ አምስት አባወራ ያሉባቸውን አራት መንደሮችን አጥንተው የታዘቡትን ሲነግሩን “…የሚገርመው ነገር በሶስቱ ጎጦች ያሉ ገበሬዎች መቶ በመቶ እዳ አለባቸው። በአንዱ ጎጥ ሶስት ሰዎች ብቻ እዳ የሌለባቸው አገኘሁ… የህውሀት መሪዎች ግን 4.3 ሚሊየን የሆነውን የትግራይ ህዝብ አንጡራ ሀብት በእጃቸው ለማስገባት ብለው ያቋቋሙት የደደቢት ፍትሀዊ ብድርና ቁጠባ፤ ፍትሀዊ ሳይሆን የትግራይን ህዝብ ግብኣተ መሬት ያስገባ እና ህዝብ፤ አባትና ልጅ፤ ባልና ሚስት የበታተነ፡ የህውሀት የንግድ ድርጅት ነው…” በማለት ነበር ቁኝ ቁልጭ አድርገው የትግራይን ህዝብ ሰቆቃ ያቀረቡት።…አቶ አስገደ።
ውድ አንባቢያን ከዚህ በታች እንደ አባሪ አድርጌ የማቀርበው ሰነድ የግንቦተ ሰባት ድረገጽ ይዞት የወጣ ሲሆን በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ያሉትን ባለሀብቶች ያመለክታል። በዚያውም ነገሩ ሁሉ ወዴት እንደሚያመራ ግንዛቤ ያስጨብጣል። ልብ ብላችሁ ተመልከቱት።
Full List of TPLF Companies Under EFFORT
Companies with investment capital of < 20,000,000 Million Ethiopian Birr
|
Company Name |
Year Est.(EC) |
Capital |
HQ |
Board Chairman |
|
Selam Transport |
1995 |
10,000000 Birr |
Mekele |
Arkebe Ekubay |
|
Segel Construction |
1995 |
10,000,000 Birr |
Mekele |
Araya Zerihun |
|
Mega Net Corp |
1995 |
10,000,000 Birr |
Mekele |
Alemseged Gebreamlak |
|
Hitech Park Axion Association |
1995 |
10,000,000 Birr |
Mekele |
Shimelis Kinde |
|
Fana Democracy plc |
1995 |
6,000,000 Birr |
Mekele |
Negash Sahle |
|
Express Transit |
1995 |
10,000,000 Birr |
Mekele |
G/selassie Gidey |
|
Ethio Rental Axion Association |
1995 |
10,000,000 Birr |
Mekele |
Atkilit Kiros |
|
Dilate Brewery |
1995 |
15,000,000 Birr |
Mekele |
Kahsay TewoldeTedla |
|
Dessalegn Caterinary |
1995 |
15,000,000 Birr |
Mekele |
Dr, Maru Erdaw |
|
Addis Consultancy House |
1995 |
10,000,000 Birr |
Mekele |
Sibhat Nega |
|
Birhane Building Construction |
1995 |
10,000,000 Birr |
Mekele |
Bereket Mazengiya |
|
Total Capital |
|
116, 000,000 birr |
|
|
Companies with investment capital between 20-49 Million Ethiopian Birr
|
Company Name |
Year Est (EC) |
Capital |
HQ |
Board Chairman |
|
Sheba Tannery Factory Axion Assoc. |
1995 |
40,000,000 Birr |
Wukro |
Abadi Zemu |
|
Meskerem Investment |
1995 |
40,000,000 Birr |
Axum |
Tewodros Ayes Tesfaye |
|
Africa Insurance Axion Association |
1995 |
30,000,000 Birr |
A.Ababa |
Yohannes Ekubay |
|
Global Auto Sparepart |
1995 |
26,000,000 Birr |
A.Ababa |
Teklebirhan Habtu |
|
Experience Ethiopia Travel |
1995 |
26,000,000 Birr |
Mekele |
Tony Hiki |
|
Addis Engineering Consultancy |
1995 |
25,000,000 Birr |
A.Ababa |
Arkebe Ekubay |
|
Hiwot Agriculture Mechanization |
1995 |
25,000,000 Birr |
Mekele |
Yohannes Kidane |
|
Berhe Chemical Axion |
1995 |
25,000,000 Birr |
Mekele |
Abadi Zemu |
|
Rahwa Yebegina Fiyel Export |
1995 |
25,000,000 Birr |
Mekele |
Yassin Abdurahman |
|
Star Pharmaceuticals |
1995 |
25,000,000 Birr |
Mekele |
Arkebe Ekubay |
|
Tesfa Livestock |
1995 |
20,000,000 Birr |
Mekele |
Yohannes Kidane |
|
Total Capital |
|
307,000,000 Birr |
|
|
Companies with a paid-up capital of >50.000.000 Million Ethiopian Birr
|
Company Name |
Year Est.(EC) |
Capital |
HQ |
Board Chairman |
|
Almedan Garment Factory |
1995 |
660,000,000 Birr |
Mekele |
Abadi Zemu |
|
Mesfin Industrial Company |
1995 |
500,000,000 Birr |
Mekele |
Arkebe Ekubay |
|
Mesob Cement Factory |
1995 |
240,000,000 Birr |
Mekele |
Abadi Zemu |
|
Almeda Textile Factory |
1995 |
180,000,000 Birr |
Mekele |
Abadi Zemu |
|
Sur Construction |
1995 |
150,000,000 Birr |
A.Ababa |
Arkebe Ekubay |
|
Trans Ethiopia |
1995 |
100,000,000 Birr |
Mekele |
Shimelis Kinde |
|
Dedebit Saving & Loan |
1995 |
60,000,000 Birr |
Mekele |
Atkilit Kiros |
|
Ezana Mining Development |
1995 |
55,000,000 Birr |
A.Ababa |
Tewodros H. Berhe |
|
Addis Pharmaceuticals Production |
1995 |
53,000,000 Birr |
A.Ababa |
Abadi Zemu |
|
Tana Trading House Axion Association |
1995 |
50,000,000 Birr |
A.Ababa |
Sibhat Nega |
|
Total Capital |
|
1,868,000,000 Birr |
|
|
Companies that did not make their paid-up capital public
|
Ambassel Commerce |
Dinsho Share Company |
Tigrai Tagai Association |
Brook Chemical Share Company |
|
Dashen Beer Factory |
Express Ethio Travel Service |
Tigrai Development PLC |
Computer Networking Technology |
|
Amhara Meleso MaquaQuam |
Berhan Building Construction |
Star Pharmaceutical Importers |
National Electromechanical |
|
Saba Emnebered |
Guna Trade Services |
Biftu Dinsho |
Oromia Credit Bank |
|
Adwa Flour Factory |
Wendo Trading |
Shala Advertisement |
National Geo-Textile |
|
Trans Ethiopia |
Tikal Agri Tigrai |
Wegagen Bank |
Alage Forest Products |
|
Sebhat Nega PLC |
Addis Transport |
Walta Industry |
Martha poultry |
|
Dima Honey Processinf plant |
Zeleke Agricultural Mechanization PLC |
Tikur Abbay Transport |
Beruk Tesfa Plastic Factory |
|
Aberdele Animal Export Company |
Maichew Particle Board |
|
|
These 66 companies are owned and managed by ethnic Tigreans
*Some Board Chairmen might have moved within the parastatals
*The amount shown on the tables above are initial start up capitals. The total networth of the parastatals has quadrupled
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



