ለዚህስ ማን ነው ተጠያቂው?

ነቢዩ ሲራክ

ይህ የምትመለከቱትን ፎት ያነሳሁት በጅዳው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኝ የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች አንድ ጽህፈት ቤት ውስጥ ነው። ይህች የምታይዋት እህትም ምን እዚያ አመጣት እንዳትሉ! ከአንድ ወር ከሳምንት በፊት በኮንትራት ስራ ከሀገር ቤት የመጣች መሆኗን ሳውዲው የእድሜ ባለጸጋ አሰሪዋ ተነገረውኛል። እኔም ሆንኩ ይህንን ጉድ አብረውኝ የሚመከቱ እህቶቸ ሁላችንም ወደ ሃገር ቤት የሚሸኙ ዘመዶቻችንና ወዳጆቻችን አጅበን ነና የመጣነው የዚህች እህት ወደ አየር መንገዱ ለምን እንዳመጣች መጠየቅ አላስፈለገኝም። በሰውነቷ ላይ ባረፈውን እስራትና ድብደባ ከመገለ እጇና ገላዋ ላይ ሰንበር የመሰለ የጉዳት ምልክት ይታያል።

 

እኒህ የተረገሙ አሰሪዎችዋ ይህች የኮንትራት ሰራተኛ እህት ይህንን በደል ተሸክማ ወደ ሃገር ቤት ለመሰደድ እንድትችል ሲሸፋፍኑ ፈጠሪ አጋለጣቸው። ይህን የታዘቡት ኢዮጵያውያን ነብሮቹ እህቶች ነበሩ። ይህችን እህት ቀርበው ጠየቋት። የደረሰባትን በደል እያነባችና እጆችዋን እያሳየች ገለጸችላቸው። በአየር መንገዱ ወደ ሃገር ቤት ሰው ለመሸኘት የመጡት እኒህ እህቶች ብዙም ሳይቆዩ አሰሪዎቿን አፋጠው ወደ ፖሊስ ወሰዱት … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ