ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ 

ወደ መጣሁባት ምድር 

እስክመለስባት በፍቅር

ሰውን ከማስደሰት በቀር

አይወጣኝም ክፉ ነገር፤

 

ልዕልት ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ነበረች በጥዑመ ዜማ የታጀበውን ይህንን ግጥም ያንቆረቆረችው። አዎ! ሠው በምድር ቆይታው ለአምሳያው ሠው መልካም ነገሮችን አበርክቶ፤ በፍቅርና በሠላም ኖሮ ማለፍ ከቻለ እንደምን ያለፀጋና መታደል ነው?! ፀጋነቱም መልካም ምግባሩና በፍቅር የተገነባው ሰብዕናው ስሙን ከመቃብር በላይ ህያው ማድረጉ ብቻም ሳይሆን ግዑዝ አካሉ ሞትንም ድል ነስቶ ለቋሚው የህይወት መምህርና የመልካምነት ተምሳሌ ሆኖ ከዘመን ዘመን፤ ከትውልድ ትውልድ መሻገር መቻሉም ጭምር እንጂ።

 

 የተምሳሌነቱና የትውልድ መምህርነቱ ግዝፈቱ፤ ጥልቀቱና ስፋቱ ቢለያይም ቅሉ፤ ሠብዓዊ ፍጡር ሁሉ በምድር ቆይታው የአቅሙንና የችሎታውን ያህል ለሌሎች ቅን አሳቢ፤ መልካም አድራጊ፤ የፍቅር የሠላምና የአንድነት ሠንደቅ ተሸካሚ… ሆኖ ቢያልፍ ዓለም ምንኛ በተለወጠች ነበር? በተለይ እኒህን ሁሉ ለማድረግና ህዝብና ሀገርን ለመለወጥ የህይታቸው ኡደት ዕድሉንና መድረኩን ያመቻቸችላቸው የሀገር መሪዎች?(ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ