ካሳሁን ዓለሙ ወልዴ

‹የጥንታዊ ኢትዮጵያን ጥበብ› የሚዳስሱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ስውተረተር ‹Encarta 2009›ን ስለኢትዮጵያ ፍልስፍና ምን እንደያዘ ጠየቅኩት። የአውሮፓ ነው ያለውን ከጥንታዊት ግሪክ ጀምሮ እስከ ዘመናዊ አሜሪካ ድረስ ያሉ የፍልስፍና ዓይነቶችን ዘርዝሮ አቀረበልኝ፤ ወደ ህንድና ቻይናም ሔዶ አማረጠኝ፤ ወደ መካከለኛው የእስልምና ዓለም ፍልስፍናም ወስዶ አስጎበኘኝ። ሆኖም ምንም እሱ በዚህ መልክ ቢያማርጠኝም እኔ ‹ጥያቄዬ አልተመለሰም› አልኩት፤ ሐቀኛው Encarta እንኳን በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በአፍሪካ ፍልስፍና መኖሩን እንዳማያውቅ እቅጩን አረዳኝ። ይህም የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶክተር አክሊሉ ሀብቴ የተናገሩትን አስታወሰኝ።

 

 

ዶ/ር አክሊሉ ለአሜሪካን ኮንግረስ የአፍሪካ ክፍል በአቀረቡት የመወያያ ሐሣብ እንዳሉት ከሆነ በእ.ኤ.አ. 1958 በካይሮ ላይ ‹Mutual appreciation of western & Eastern cultural values› በሚል ርዕስ በተካሔደ ጉባኤ የአፍሪካ አስተምህሮ አለመነሳቱ አስገርሟቸው ‹አፍሪካ የት ናት?› የሚል ጥያቄ ለመጠየቅ መገደዳቸውን አንስተው፤ የተሰጣቸው መልስ ‹አፍሪካ ያላት መኃይም ማኅብረሰብ ነው› የሚል ዓይነት እንደነበር ገልጸው ነበር። እኔም Encarta ሐቀኛ መልሱን ከነገረኝ በኋላ የበለጡ ጥያቄዎች ተግተልትለው መጡብኝ። ‹ለምን የእኛ ዕውቀት ሳይመዘገብ ቀረ?› የሚል! ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ