ምርኮኛ - ቅኝት መስፍን ማሞ ተሰማ (ሊያነቡት የሚገባ)
የመጸሐፉ ደራሲ ቆንጅት ብርሃን
መንደርደሪያ
ደምና ዕንባ ተቀላቅሎ በብዕር ሲቀሰም ምንን ይወልዳል? ምርኮኛ! ምርኮኛ የደም መፅሀፍ ነው። የዕንባ መፅሀፍ። የአንድ ትውልድ ደም፤ የአንድ ትውልድ ዕንባ የተተረከበት የደም ዕንባ ታሪክ። ምርኮኛ አንባቢን ምርኮኛው አድርጎ በትርክቱ ባህር እየደፈቀ፤ ትንፋሽ እስኪያጥር ነፍስ እስክትቃትት አካልና መንፈስን ረግጦ የሚገዛ፤ ሃያል የደም ዕንባ ታሪክ ነው - ያልታደለው ትውልድ ታሪክ።
ምርኮኛ በተደራሲ ነፍስያ ውስጥ የራሱን ነፍስያ ፈጥሮ እስከወዲያኛው የሚኖር ረቂቅ ህዋስ ያለው የትውልድ ታሪክ ትሩፋት ነው - ማን ይመስክር የነበረ፤ ማን ያርዳ የቀበረ - እንዲሉ ጥንታውያኑ። እና ምርኮኛን አንብቤ የአካልም የህሊናም ምርኮኛ ሆኜ ሰነበትኩ። ታሪከኞቹ ሲታገሉ ታግዬ፤ ሲታሰሩ ተቀፍድጄ፤ ሲገረፉ አቃስቼ፤ ሲረሸኑም ህቅ ብዬ - ነፍሴን ከስጋዬ ለይቼ። ኖርኩት ያንን ዘመን ዳግም ተወልጄ፤ ወጣትነቴን ምርኮኛ ውስጥ አግኝቼ።
ምርኮኛ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ አንድ ምዕራፍ የጨበጠውን የታሪክ ክስተት የሚያትት ነው። ዘመነ ኢሕአፓን። መቼም ‘ፍርድ እንደራስ ነው’ እንዲሉ፤ ምርኮኛን ያላነበባችሁ መፅሀፉን አንብባችሁ ትፈርዱ፤ ያነበባችትሁም ሀቁን ትመሰክሩ ዘንዳ - እነሆኝ ምርኮኛ። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)



