የኃየሎም አርአያ አሟሟት… እና በጀሚል ያሲን ላይ የተሰጠ የሞት ብይን (ክፍል 2)
በዳዊት ከበደ ወየሳ - አትላንታ
አንዳንድ ወዳጆቻችን ባለፈው ሰሞን ባወጣሁት የኃየሎም ግድያ ዙሪያ ቅሬታቸውን ገልጸውልኛል። ሆኖም በኔ ውስጥ ያለውና እነሱ የሚሉት እውነት አይገናኝም። ለነገሩ ብዙዎቹ ዘገባዎች ሀገር ቤት እያለሁ ያወጣኋቸው ናቸው። ይሄንን ጽሁፍ ለየት የሚያደርገው ዝርዝር ትንታኔ ውስጥ በመግባቴ ነው። አሄንም ቢሆን በእኔ እምነት ነገሮችን በመሸፋፈን የምንሄድበት መንገድ ሌሎች እውነቶችን እንዳንመለከት ያደርገናል። ምንም እንኳን ጀሚል ያሲን ግድያውን ቢፈጽምም፤ የተደረገበትን ኢሰብአዊ ተግባር አልደግፍም።
ለምሳሌ ንብረቶቹ አለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በወያኔ ባለስልጣናት ተመዝብሯል። እና የፈለግነውን ያህል ኀየሎምን ብንወደውና ጀሚልን ብንተላው ቢያንስ ወያኔ ያደረገውን ግፍ በመደበቅ የምንሄድበት መንገድ ማንን እንደሚጠቅም አይገባኝም።እኔም ብሆን ይህንን ጉዳይ እንደገና ለማንሳት የተገደድኩት… ይህ የጀሚልና የኃየሎም ጉዳይ ነፍስ ተሰጥቶት የህዝቡ መነጋገሪአ በመሆኑ ነው እንጂ፤ ጉዳዩ ከጀሚል ጋር እንደሞተ ከኔም ጋር ሊሞት ይችል ነበር። ሆኖም የኃየሎም አሟሟት ሲነሳ ሻእቢያን እያገዘፉ… የወያኔንም ግፍ እየደበቀ መሄዱ በኔ እምነት የትም የሚያደርስ አይደለም።
ስለሆነም በዚህ እኔ በምጽፈው ታሪክ ምክንያት ልዩነት ሊኖረን ይችላል። ይህ ግን በመካከላችን እንደ መሰረታዊ ችግርና ልዩነት መቆጠር የለበትም። የማውቀውን እውነት በመናገር የወያኔን የተደበቀ ግፍ በመጻፌ የሚቀየሙኝ ካሉ ግን ከአቅሜ በላይ በመሆኑ፤ እኔ እየወደድኩ እነሱ ሊጠሉኝ ይችላሉ። እዚያ ላይ ምንም ቁጥጥር የለኝም። ለሁሉም ግን በማውቀው እውነት ላይ ቆሜ የወያኔን ግፍ ማጋለጤን እቀጥላለሁ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)



