ስም ልቀይርልህ (ማናለህ)
ስም ልቀይርልህ
ማናለህ ከአሳረኛው ሀገር ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )
እየተሳበበ በቁስቋም መባቻ፣
ቁም-ስቅልህን ካየህ በመወለድ ብቻ።
ስሙን ልቀይረው
እነብሴን፣
በሀውዜን።
ትባል እንዋሪ፣
ለጊዜው መይ ነብሪ።
ደላንታም ይሰየም፣
ተብሎ አዲጉደም።
ይቀየር ግዴለም በረንታ፣
በእንደርታ።
ሣር ምድር፣
በእሙን ሐጅር።
ጠዳና ምንዝሮ፣
ብየ ልጥራህ ይሆን ውቅሮና ሽራሮ፣
መፍትሔ ካስገኜህ አዳም ከሚያልቅ ታስሮ፣
ቆዳው ከሚነግል በጨካኝ ቁፋሮ።
ታዲያ ምናጠፋህ
ምናልባት ችግሩ ከስሙ ከሆነ፣
ብየ ልጥራው እንጂ አጥሌን በርሃነ።
ይግዘውም ይጠራ በመባል ስብሃት፣
አንጓችም ሁናለች ከእንግዲህ አብርኸት፣
አምላክ እስኪያበርደው ይህን የዘር እልቂት።
ማናለህ ከአሳረኛዉ ሀገር ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )



