ኦባማ (የአፅብአሔ)
"ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፦እርሱ የማዕዘን እራስ ሆነ፣
ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፦ ለዓይናችንም ድንቅ ናት።"
መዝ. 17. 117 ቁ 22-23
ኦባማ
ከየአፅብአሔ (በርን - ስዊትዘርላንድ 2008/11/8)
ኦባማ ኦባማ ኦባማ ኦባማ
ነፃነት ለራበው ፍትህ ለተጠማ ...
ምድሪተቱ ጨቅይተተ
ተበክላ በደም
በዘር በኃይማኖት
ሲጨፋጨፍ ዓለም
ግፍ ሞልቶ ፈሶ
ቢወጣ ከሰማይ
የአምላክ ዓይንአረፈ
መርጦት ኦባማ ላይ።



