የሰው አውሬ! (አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ)
አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ
አውሬነቱን ያልጨረሰ
ከ’ጭራቅ’ የባሰ!
እንደ በግ ፍሪዳ
ሰው አርዶ የሚበላ
የሰው ደም የተጠማ
እርኩስ ወራዳ
ለካ ’የሰው አውሬ’ አለና
በደቡብ አፍሪካ!
ይህን ጉድ ሳያይ
ይህን ስቃይ፤
እንኳን ሞተ! ተቀበረ!
ማንዴላኮ ሰው ነበረ!!!
፨ ፨ ፨ ፨ ፨
መታሰቢያነቱ@ በደቡብ አፍሪካ ለተሰዉ ወገኖቻችን @
አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ (Assefa GMT.)
April 20, 2015, Las Vegas, NV.



