Abera Lemma and yehamerewa qonjo ጋዜጠኛ አበራ ለማ ከሐመሯ ቆንጆ ጋራየወለላዬና የአበራ ለማ የግጥም ምልልስ

ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሬድዮ ጋዜጠኛ በነበረበት ጊዜ ወደ ጋሞጎፋ
ለሥራ ሄዶ ሳለ፣ በድንገት ካጋጠመችው የሐመር ቆንጆ ጋር የተነሳው ፎቶ ነው። ዘመኑ 1969 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፎቶ ግራፍ አንሺው የእርዳታ ማስተባበሪያው ማንተጋፍቶት አጥናፉ ነበር። ምልልሱን ያንብቡ!

 

በደመቀ ፀሐይ
ወለላዬ

በቀን አጋማሽ ላይ |- በደመቀ ፀሐይ
አካሏ ተጋልጦ - በግማሽ የሚታይ፣
የተዋበች ሐመር - መንገድ ላይ ብትወጣ
አዬ ጋዜጠኛው - የመጣበት ጣጣ፣
እሷ ግን እቀፊው - ሳሚው ሳሚው ብሏት
ጎኑ ብትጠጋው - አሹላ ያንን ጡት፣
የሱም አጉል ፍራት - የሷም አጉል ድፍረት
በደመቀ ፀሐይ
ሰውም ይፈራል ወይ?

 

ምነዋ አልፈራ
አበራ ለማ

ጌታ ወለላዬ - ምነዋ አልፈራ
መትረየስ ደግና - ፊቴ ተገትራ፤
ደ’ሞኮ አወጣጧ - ከጫካው ከዱሩ
መፍራት ይነሰኝ ወይ - እንግዳው ላገሩ፤
አያድርስ እንጂ ነው - touch down ብትለኝ
በዚህ በጠራራ - መጋኛስ ቢመታኝ፤

 

ታዝቤህ ነበረ
ወለላዬ

ዘምተህ የተመለስክ - በናቅፋ ተራራ
መሳሪያ የጨበክ - ከጀግኖቹ ጋራ፣
ባዶዋን የመጣች - ኮረዳ ስትፈራ፣
ታዝቤህ ነበረ - ጋዜጠኛ አበራ።
አሁን ግን ሳስበው - ነገሩን በትኩረት
ጠላትን ሰብስቦ - ማርኮ ለማስቀረት፣
ወታደር መልምሎ - ጦር ሜዳ ከማዝመት
ሳትሻል አትቀርም - አንዷ የሐመር ሴት፣

 

ያልተነካ …
አበራ ለማ

አወይ አለመያዝ - አለመነካት
ጡር ነው ወለላዬ - በነፍሴስ መምጣት፤
ጥግብ ፍርጥም ያለች - ደንደሮ ወጣት
ታስጨፍረኝ ነበር - ኢቫንጋዲ ስልት፤
ናቅፋ ቢበረታም - ይሄ ጋዜጠኛ
ከመሆን አልዳነም - የሐመር ምርኮኛ!!!!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ