ጫፍና ጫፍ (አትክልት አሰፋ)
ሁለት ጫፍና ጫፍ ያልተገጣጠመ፣
አንደኛው ቀና ሲል፤ ሌላው ያዘመመ፤
አቅጣጫ ሲፈልግ ጫፉ ለመጋጠም፣
ይሄኛው ሲራወጥ ከዚያኛው ሊጣጣም፣
አንዱ በዚህ ሲዞር፤
ያኛው ወዲያ ሲያከር፣
የሚያለዝብ ጠፍቶ፤
በየፊናው ሲበር፤
ምኞታቸው ሳይሰምር፤
ፍላጎት ሳይረካ፣
ወዲያ ወዲህ ሲሉ ጫፍ ሳይነካካ፤
ይሄን ጫፍ ከዚያኛው ማጋጠም ቢችሉም፣
ሁሉም ቢዳክሩም መፍትሄ አላገኙም።
ጥሞና ሳይሰፍን በመሀከላቸው፣
ፍላጎት ብቻውን ሲነድ በሆዳቸው
ሁለቱም አንድ ሆነው፤ ሃሳብም ሳይሞላ፣
መክነው እንዳይቀሩ በሉ እንፍጠር መላ።
ፌብሪዋሪ 8/2014 ቫንኩቨር (በርናቢ)



