ህቡዕ ስሜት (ምኒሊክ ኃይለማርያም)
ምኒሊክ ኃይለማርያም
ባንተም - በኔም ስር ያለው
ከደምህ ውስጥ ሚተነው
በደሜ ውስጥ ሚሰርጸው
ያ ትኩሳት
ህቡዕ ስሜት
ካጥንቶችህ ከወገኖችህ -
ተቆንጥሮ
ለህዋሳቴ የተቸራት
ስሟ ሲጠራ ሚያነዝረኝ
ኢትዮጵያ ብለን ስንዘክራት።
ምኒሊክ ኃይለማርያም
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



