የፓፓው ምርጫ
ቦጋለ ዳኜ
የፓፓውን ምርጫ ሲጠብቁ ሲጠብቁ፤
ነጭ ጪስ ዐይተው ከሩቁ፤
ሰምተው ሲደወል መጥቁ፤
ገና ማን ይመረጥ ሳያውቁ፤
ምርጫው በመጠናቀቁ፤
በመላው ዓለም ካቶሊኮች ፈነደቁ!
ከዚህ ከዚያ ሳይባል ዘሩ፤
ጸላዔ ሠናያት ሳይገባ በነገሩ፤
የት ነው ሳይባል አገሩ መንደሩ፤
እጮዎች ሲወዳደሩ፤
ሲመረጡ ሲንጠረጠሩ፤
ገና ነው ሲል ጪሱ ጥቁሩ፤
በመጨረሻ ተመረጠ ጳጳስ!
ጨሰ ነጭ ጭስ!
ባለዕጣውም ጳጳስ ታወቁ።
ብቅ ብለው ታዩ አበቁ ።
ደስታውም ቀጠለ ካቶሊኮች ፈነደቁ።
ፖፕ ቤኔዴክትም በክብር ለቀቁ።
ቦጋለ ዳኜ
ከካሊፎርንያ



