ያቶ መለስ ነገር ግራ የሚያጋባ

ሬሳቸው አድዋ ሳጥኑ አዲሳ አባ

 

ጌታው አቶ መለስ በቁም ሰው የፈሩ

ሞተው ባደባባይ መታየት ጀመሩ

 

አወይ አቶ መለስ የብልጦቹ ቁንጮ

ቀብራቸው ሆነ አሉ በእንባ መዋጮ

 

መች በንባ አበቃና የሳቸው ቀብር

መዋጮው ቀጥሏል ከድሃው ቤት ብር

 

በቁማቸው ሳሉ እድር መግባት ትተው

አወይ ንፉግ ጠባይ ቀባሪ አሳጣቸው

 

ጌታው አቶ መለስ ለሰሩት ሥራቸው

በላይኛው መንደር የት ይሆን ቤታቸው

 

 

አስለቃሿ ስትገጥምና ህዝቡ ሲቀበል  እንደዚህ ይመስለኛል ግን እርገጠኛ አይደለሁም፤

 

(ህዝቡ)   ዋይ ዋይ !

(አስለቃሽ)   ዋዬ ወየው !

(አስለቃሽ)   ያቶ መለስ ነገር ግራ የሚያጋባ

(ህዝቡ)   ዋይ ዋይ !

(አስለቃሽ)   ዋዬ ወየው !

(አስለቃሽ)   ሬሳቸው አድዋ ሳጥኑ አዲሳ አባ

(ህዝቡ)   ዋይ ዋይ !

(አስለቃሽ)   ዋዬ ወየው !

………………………………………..

…………………………………………….

……………………………………………..

(ህዝቡ)   ውይ ! ውይ !ውይ !ውይ ! ውይ !

(አስለቃሽ)   እንዲያ !

 

እርገጠኛ ስላልሆንኩ፤ በእድሜ ጠና ካሉ እህቶቻችን ጠይቀህ አርሙና፤ ከተቻለም ሌሎች ግጥሞችን ጨማምራችሁ፤ እንደገና ጻፉና፤ « አስለቃሹ » በሚል የብእር ስም ከመለስ የቀብር ቀን በፊት በአስቸኳይ በተለያዩ ድረ ገጾች በትኑት ::

እኛ በነጻው አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን በግድ አልቅሱ ተብለው ለሚጨነቁ ወገኖቻችን መብት ዘብ የመቆም ግዴታ አለብንና አደራ ::

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ