ታፔላ (ተለጣፊ) ስም በመስጠት በኢትዮጵያችን ታሪክ ወደር ያልተገኘለት የወያኔ/ኢህአዴግ በቅርቡ ”ሽብርተኛ” በሚል ታፔላ (ተለጣፊ) ስም በርካቶችን ለእስር እየዳረገ እንደሆነ ይታወቃል። ለነፃነት ትግል የሚያደርጉትን ፖለቲከኞችን፣ አርቲስቶችን፣ ነፃ ጋዜጠኞችን፣ ሲቪል ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን የውጭ ሀገር ጋዜጠኞችን ጭምር ”ሽብርተኞች ናቸው” በሚል ወደ መቀመቅ እስር ቤቱ እያወረዳቸው መሆኑን የመገናኛ ብዙኀንን ለሚከታተሉ የተሰወረ አይደለም።

 

ከእነዚህ ሰለባዎች ውስጥ ታዋቂው አርቲስት ደበበ እሸቱ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ደበበ እሸቱ ከአርቲስትነቱ ባሻገር በምርጫ 97 ቅንጅትን ወክሎ በመወዳደር ከፍተኛ የህዝብ ተወዳጅነትን ካገኙትና የኢህአዴግን ተወዳዳሪዎች በህዝብ ድምፅ ካሸነፉት አንዱ ለመሆን መብቃቱ አይዘነጋም።

 

ዛሬ በእስር ላይ ለሚገኘው አርቲስት ደበበ እሸቱ ”የመድረኩ ጀግና” በሚል ርዕስ በስዊድን የምትገኘውና ማራኪ በሚለው የብዕር ስሟ የምትታወቀው ገጣሚ የገጠመችለትን በራስዋ ድምፅ እንደሚከተለው ተቀናብሮ ቀርቧል። ለማዳመጥ የማጫወቻ ቆልፉን ይጫኑ!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ