የአቶ መለስ ጠላት
ከዘመን ተለወጠ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ተቃዋሚ ብሆን ጠላት ነው ስላሉኝ
እኔም አሜን ብዬ በስሜ መጣሁኝ
የደግ ዘመን ጠላት አሁን ወዳጅ ሆኘ
በክፉ ቀን መጣሁ ሲጨነቁ አዝኘ፥
እግዜር ያሳይዎ ይሰሙኝ በአባዜዎ
ጊዚው ቅርብ ስለሆነ የፍርድ ቀንዎ
ጨርቄን ማቄን ትተው ከነቅሌትዎ
መሰስ ቢሉ አይከፋም ከነሴትዮዎ፣
መንጌ በቀደደው ቀጭን መንገድ ዘልቀው
ሕይወትዎን በሔግ ቢቀጩ መልካም ነው፣
በምኒልክ ግቢም ታጥረው ስለኖሩ
በሔግም ቢኖሩ አንልም ታሰሩ፣
ሲያስሩና ሲፈቱ ሕይዎትም ሲሰርቁ
ሥራ በዝቶበዎት ሌትም ሲጨነቁ
ሱናሚው እንዳይደርስ ባክዎ ይጠንቀቁ፣
የሚመጣው ላይቀር ያለፈ ላይመጣ
አይልፉ በክንቱ መጫወት ገበጣ፣
ጨርቄን ማቄን ሲሉ ሰማዩ ቢጨልም
ለእኛም ደግ አይደለም እርስዎ ግን የሉም።
ከዘመን ተለወጠ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.