እኛ ግን ለውጥ የለን (ስሜነህ ታምራት)
እኛ ግን ለውጥ የለን
ስሜነህ ታምራት (ከስዊድን)
ከአዲስ ዘመን ጋራ - አዲስ ተስፋ ሳይወለድ
የታሰረው ሳይፈታ - የተፈታው ሳይራመድ
ተቻችሎ ለሀገር መሥራት - እንደባህል ሳይለመድ
አብሮ መብላት አብሮ መጨፈር - ምን ሊፈይድ
ምንስ ሊያመጣ - ምንስ ሊወስድ።
ለእግዚአብሔር ሠላምታ ደንታ የማይሰጠው
ፍቅርና አንድነት ጨርሶ የሌለው
ዘመኑ ቢለወጥ ምን ባንድ አስጨፈረው?
ህዝበ-ቃል ተከብሮ - ህዝበ-ኃይል ሲረታ
ተፈችው ሲራመድ - እስረኛው ሲፈታ
መዝለልስ ያኔ ነው - መጨፈር እስክስታ።
ዘመን ተለወጠ - እኛ እንጅ የቀረን
ለውጥን እየፈለግን - እኛ ግን ለውጥ የለን።
ስሜነህ ታምራት (ከስዊድን) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



