ብርቱካን ትፈታ! (ወለላዬ ከስዊድን)
ብርቱካን ትፈታ!
ወለላዬ ከስዊድን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
“ብርቱካን ትፈታ!” ስንል እኛ ዛሬ
ምን ያህል እንደሆን ያለን ጥንካሬ
መፈተሽ አለብን እንዳንቀር በወሬ።
ህዝብ አዳራሽ ጠርተን አድርገን ስብሰባ
መለየት ከሆነ በደማቅ ጭብጨባ
ትርፍ የለንም ጭራሽ አንበቃም ለውጤት
ለመሥራት ካልቻልን ተባብረን በአንድነት።



