አቶ አገኘው ተሻገር

አቶ አገኘው ተሻገር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

ሹመቱን የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር ናቸው

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 1, 2021)፦ የአማራ ክልል ከጸጥታና ደኅንነት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አዳዲስ ተሿሚዎችን አስቀመጠ።

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር የተሰጡት ከእነዚህ የኃላፊነት ቦታዎች የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ አንደኛው ነው። በዚህ ከፍተኛ ኃላፊነት የተሰጣቸው አቶ ሰማ ጥሩነህ ሲሆኑ፤ ይህ ኃላፊነት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ጭምር የተሰጠ ነው።

ሌላው በርዕሰ መስተዳድሩ ሹመት የተሰጠበት ቦታ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ነው። ባለፈው ረቡዕ እንደዘገብነው፤ አዲሱ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ተኮላ አይፎክሩ ናቸው

በዛሬው ይፋዊ ሹመት የአማራ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመኾን የተሾሙት ደግሞ፤ ኮሎኔል ባምላኩ ዓባይ ናቸው።

አቶ ዝጋለ ገበየሁ ደግሞ የክልሉ ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ኾነው የተሾሙ ሲሆን፤ የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ኾነው እንዲሠሩ ደግሞ አቶ ሀብታሙ ሞገስ ተሰይመዋል።

በአቶ አገኘው ተሻገር ዛሬ ሹመት የተሰጠበት ሌላው የኃላፊነት ቦታ ደግሞ፤ የአማራ ክልል የፍትሕ ማሠልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት ሲሆን፤ ይህንን ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የተሾሙት አቶ ሙሉጌታ አበራ ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ