Dr. Tedros Adhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም

ከአንድ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ተገናኝተው ነበር

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 2, 2020)፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ አንድ ግለሰብ ጋር መገናኘታቸውን በማስታወቅ፤ ራሳቸውን ማግለላቸውን ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በትዊተር ገጻቸው አሳወቁ።

በቅርብ ጊዜ ውስጥ ያገኙት ይህ ግለሰብ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት በመረጋገጡ፤ ራሳቸውን በማግለል ሥራቸውን ከቤት ኾነው ለመሥራት መወሰናቸውንም ገልጸዋል።

ጤንነታቸውን በተመለከተም በአሁኑ ወቅት ምንም ዐይነት የቫይረሱ ምልክት የማይታይባቸው ስለመኾኑ በዚሁ የትዊተር ገጻቸው ላይ አመልክተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ