Solomon Tadese

እስካሁን 17 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 22, 2020)፦ ባለፈው ዓርብ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. በቡራዩ ከተማ የደረሰውን ጥቃት በማቀነባበርና በመተግበር ተሳታፊ በመኾን የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸው እየተገለጸ ነው።

አቶ ታዬ ደንደና በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት እስከትናንት ድረስ 17 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ጠቁመው፤ ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሕግ የበላይነቱን ለማረጋገጥ ከሕዝብ ጋር የሚሠራ ስለመኾኑና ቃል የሚገባ መኾኑን ጠቅሰዋል።

ባለፈው ዓርብ የካቲት 13 ቀን ምሳ ሰዓት ላይ የቡራዩ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት ኮማንደር ሰለሞን ታደሰ ከሰዎች ጋር ምሳ እየበሉ በነበረበት ወቅት በታጠቁ ኃይሎች ተተኩሶባቸው መገደላቸውን መዘገባችን አይዘነጋም። በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩ የፖሊስ አዛዥን ጨምሮ ሦስት ሰዎች በጥይት ።

በዚሁ ጥቃት የአቶ ሰለሞን ሕይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፣ የቆሰሉት ሁለት ፖሊሶችና አንድ አርቲስት ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ