የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፳፱
አብሮ ከመቀበር
ስሩ መበስበሱን ንገሩት በይፋ
አጓጉል በመውደቅ ሰው እንዲያጠፋ
ለዚህ ነው የሚበጅ የቅርብ ሰው ምክር
እራሱም እንዲድን አብሮ ከመቀበር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





አብሮ ከመቀበር
ስሩ መበስበሱን ንገሩት በይፋ
አጓጉል በመውደቅ ሰው እንዲያጠፋ
ለዚህ ነው የሚበጅ የቅርብ ሰው ምክር
እራሱም እንዲድን አብሮ ከመቀበር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ሌላን ሊያሽቆጠቁጥ
ስሙ ያልተጠራ ሥልጣን ያልጨበጠ
አለ በየቦታው ደረቱ ያበጠ
ምንም ተራ ቢሆን የግፈኛን ፈሊጥ
ይመኛል በልቡ ሌላን ሊያሽቆጠቁጥ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የሌላ ሰው ስንጥር
ሲመታው ያደገ የግፈኛ ጥፊ
መስማማት አይችልም ሆኖ ሆደሰፊ
የሱ ሳይታየው የጨበጠው በትር
ትረብሸዋለች የሌላ ሰው ስንጥር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አንዳንዴ ተቆጣ
ከሆነ ሥራዬ የሱን ሐሳብ ማጽደቅ
አልሰበሰብም እንኳን ለጸብ፤ ለእርቅ
በልና ተናግር እንቢ ብለህ ውጣ
በእሽታ አትኑር አንዳንዴም ተቆጣ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ሽብር ተከላካይ
እኔን የሚጎዳ አዋጅ ካወጣችሁ
አልችልም ሽብርን ልመክትላችሁ
የሚለው ዘረኛ ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ
እንዴት ነው የሚሆን ሽብር ተከላካይ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





አጉራሽና ጎራሽ
በሞቴ እያለ ወደ አፍ የሚያደርስ
"ጠላትክን" እያለ ነበር የሚጎርስ
አጉራሽና ጎራሽ እንደዚህ ነበሩ
በመጉረስ በማጉረስ የሚተባበሩ
ዛሬ ተፈልጎ አንድ አጉራሽ ተገኝቶ
'ሚያጎርስ አስመስሎ ጠቅልሎ አዘጋጅቶ
ራሱ ጎረሰው ጎራሽ አፉን ከፍቶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አረጓት አክርማ
አርባ ሚንስትሮች ገንዘብ የጠገቡ
የሚያወጡት አጥተው አዋጅ የተራቡ
ዓለም ያወቃትን አንዲቷን ከተማ
ሁለት አደረጓት ከፍለው እንዳክርማ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





መስፈሪያችን አንሷል
የእነሱን ጥላቻ ጥፋትና በደል
ወደፊትም ገና ያሰቡትን ተንኮል
ለማወቅ አልቻልንም እስካሁን ጨርሶ
ማንነታቸውን መስፈሪያችን አንሶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





እንጸልይ
በእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ትርምስ
በራስ ወዳድነት ሱስ
ሕዝብ በሕዝብ ላይ!
ዘመድም በዘመዱ አዋይ!
እጁን ዘረጋ፣ ቃል እምነቱን አፈረሰ
የመጨረሻው ዘመን ደረሰ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





እርጅናሽ ወደደኝ
እናቴ ሽበትሽን በሽበቴ አየሁት
ጥርሴም እንደጥርስሽ ረግፎ ሸኘሁት
እንደአንቺው ደፋ አለ ወገቤም ጎበጠ
እርጅናሽ ወደደኝ ካንቺ የበለጠ
ሙሉውን አስነብበኝ ...