Mekelle University

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ

የወላጅ አንጀት ነውና በአደባባይ ማንባታቸው የሚጠበቅ ነው

ትዕግሥት መንግሥቴ (ኢዛ)

በትግራይ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ጉዳይ ዛሬም አሳሳቢ ነው። የተማሪዎቹ ወላጆች ልጆቻችንን እያሉ ነው። የወላጅ አንጀት ነውና በአደባባይ ማንባታቸው የሚጠበቅ ነው። ምክንያቱም ተማሪዎቹ ያሉበት አካባቢ ከፍተኛ የደኅንነት ሥጋት ያለበት በመኾኑ።

በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን አንዳንድ ታጣቂዎች በክልሉ በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች ውስጥ ገብተው እየፈጸሙ ነው ተብሎ የሚነገረው ተግባር አይደለም ልጆች ያላቸው፤ ሌላውንም የሕብረተሰብ ክፍል የሚረብሽ ነው።

በሌላ አንጻር ደግሞ እንደ ማይጨው ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች ደግሞ በሰሞናዊው አዲስ ችግር ሥጋት ገብቷቸው፤ በእግራቸው አሳብረው ወደ አማራ ክልል መግባታቸው ተሰምቷል። ስለዚህ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ያሉት ተማሪዎች ደኅንነት ማሥጋቱ አይቀርም።

ሰሞኑን ወላጆች ስለልጆቻቸው ጉዳይ በጠየቁበት ወቅት ተማሪዎቹን ከዚያ ለማስወጣት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑ ነው። ከዚህ መረጃ በኋላ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፤ ተማሪዎቹ በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኙ መኾኑን፤ እንዲሁም የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ያሉ እንዳሉ ትናንት (እሁድ ሰኔ 27 ቀን 2013 ዓ.ም.) አሳውቋል። ወላጆችም ይህንን አውቀው በመንግሥት የተጀመሩ ጥረቶችን እንዲደግፉም ጥሪ አቅርቧል።

በትናንትናው ዕለት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለተማሪዎች ቤተሰቦች በማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ሳይቋረጡ እያከናወኑ መኾናቸውን ነው።

ይህንን ትግራይ ውስጥ ከሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ባደረገው ክትትል ያረጋገጠ መኾኑንም አሳውቋል።

“የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በቦታው በመገኘት የተማሪዎችን ድምፅ በመቅረጽ፤ ለተማሪ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማሰማታችሁ እና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እየሰጠ ያለውን መረጃ በተጨባጭ ማስረጃ ስላረጋገጣችሁ እናመሰግናለን!” የሚል መልእክትም በመረጃ ገጹ አስፍሯል።

ተማሪዎቹ በጥሩ ሁኔታ ላይ መኾናቸው መልካም ዜና ነው። ነገር ግን ተማሪዎቹን በተቻለው ፍጥነት ከትግራይ ክልል ማስወጣት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያ ዛሬም ይህንን መድረክ በመክፈት ሐሳቦችን ታስተናግዳለች ብዬ አምናለሁ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ