EPRDF press release on TPLF

ከኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

“ኢሕአዴግን ከግንባርነት ወደ ውሕድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ሲነሳ የቆየ ጥያቄ ነው” ኢሕአዴግ

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 18, 2019):- ኢሕአዴግን ውሕድ ፓርቲ ለማድረግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱ እየተገለፀ ባለበት ወቅት፤ ሕወሓት ውሕደቱን እንደማይቀበልና ከዚሁ ጋር አያይዞ ያወጣው መግለጫ የፓርቲውን አሠራር የጣሰ መኾኑን የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ከኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ ሕወሓት እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አቀንቃኝ ኾኖ ሒደቱን ሲመራ እንደነበር በማስታወስ፤ አሁን በውሕደቱ ዙሪያ እያወጣ ያለው መግለጫ ተገቢ እንዳልኾነ አመልክቷል።

“ኢሕአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ሕብረ ብሔራዊ ውሕድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ በ1996 ዓ.ም. ከተካሄደው 5ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጀምሮ በተከታታይ በተካሄዱት የድርጅቱ ጉባዔዎችና የተለያዩ ድርጅታዊ መድረኮች ሲነሳ የቆየ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል” በማለት ሕወሓትም ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የውሕድ ፓርቲውን የመመሥረት ዓላማው አቀንቃኝ እንደነበር ኢሕአዴግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ከውሕደቱ በፊት እንዲህ ያለ መግለጫ መሥጠት ተገቢ ያለመኾኑን የሚያወሳው የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት መግለጫ፤ ኢሕአዴግ ወደ ውሕድ ፓርቲ ለመለወጥ የተፈለገባቸውን ዋና ዋና ነጥቦች በዚሁ መግለጫው ላይ አካትቷል።

ዛሬ ማምሻውን የወጣውን የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! ኢዛ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ