ኢሕአዴግ ሕወሓት ላይ መግለጫ አወጣ

EPRDF press release on TPLF

“ኢሕአዴግን ከግንባርነት ወደ ውሕድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ሲነሳ የቆየ ጥያቄ ነው” ኢሕአዴግ

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 18, 2019):- ኢሕአዴግን ውሕድ ፓርቲ ለማድረግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱ እየተገለፀ ባለበት ወቅት፤ ሕወሓት ውሕደቱን እንደማይቀበልና ከዚሁ ጋር አያይዞ ያወጣው መግለጫ የፓርቲውን አሠራር የጣሰ መኾኑን የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦዴፓ “ኢሕአዴግ ሲያራምደው የነበረው አብዮታዊ ዴሞክራሲ በቃው!” አለ

TPLF and ODP

ለሕወሓትና ለአብዮታዊ ዴሞክራሲያውያን የተሰጠ መግለጫ

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 18, 2019):- የኢሕአዴግ አወቃቀር ሲመራበት የነበረው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሕዝብን ውሳኔ ሰጪነት የሚገድብ ስለኾነ ለደረስንበት የትግል መድረክ የሚመጥን አለመኾኑን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘምዘም ባንክ የመጀመሪያው ከወለድ ነፃ ባንክ ሆኖ ሥራ ሊጀምር ነው

Zamzam Bank

በሸሪዓ ሕግ የሚሠራ የመጀመሪያው ከወለድ ነፃ ባንክ ይኾናል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 17, 2019):- ራሱን የቻለ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመሥጠት የሚያስችል ባንክ ለማቋቋም ሲንቀሳቀስ የቆየው ዘምዘም ባንክ አክስዮን ማኅበር፤ ወደሥራ ለመግባት የሚያስችለውን ካፒታል ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ክልል የፀጥታ ስጋት ባለባቸው ቦታዎች የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ፈቀደ

Amhara region

“አሁን ያለው ሁኔታ ለክልሉም ኾነ ለመላው አገሪቱ የፀጥታ ስጋት ወደመኾን ተሸጋግሯል” የደኅንነትና የፀጥታ ካውንስሉ

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 17, 2019):- ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በቅማንት ብሔረሰብ ማንነት ጥያቄና በተያያዙ ምክንያቶች የሚታየውን የፀጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መወሰኑንና በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ የአማራ ክልል ደኅንነትና የፀጥታ ካውንስል የጋራ ውሳኔ አሳልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሽያጭ የተዘጋጀው ኢትዮ ቴሌኮም ገቢው እየጨመረ ነው

Ethio Telecome

በአፍሪካ በደንበኞች ቁጥር ይመራል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 17, 2019):- በከፊልና ሙሉ ለሙሉ በሽያጭ ለግል ኩባንያዎች ከሚሸጡ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ በቀዳሚነት የተቀመጠው ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ደምበኞቹን ቁጥር ከ51 ሚሊዮን በላይ ሲያደርስ፤ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት (በሦስት ወር) ጊዜ ውስጥ ከ10.1 (አሥር ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት ችሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጠንካራ ውሳኔ ያሳልፍበታል የተባለውን ስብሰባ ጀመረ

Lemma Megerssa honouring Abiy Ahmed

ለሕወሓትም ምላሽ የሚሠጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 16, 2019):- በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው በወቅታዊው ክልላዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚመክር ሲሆን፣ የተለያዩ ውሳኔዎች የሚተላለፉበትና ለሕወሓትም ምላሽ የሚሠጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕወሓት ከውሕደቱ ውጭ ነኝ አለ

TPLF press release

“በውሕደት ስም በፍጹም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ መንገድ አዲስ አሃዳዊ ድርጅት ሊመሰረት አይገባም” ሕወሓት

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 15, 2019):- ኢሕአዴግን ወደ አንድ ውሕድ ፓርቲ ለማምጣት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የማይቀበል መኾኑን ሕወሓት በይፋ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ዛሬ በ10 ሺህ ብር ዋስ ተለቀቁ

BG Tefera Mamo and Col. Alebel Amare

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 14, 2019):- ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያና “መፈንቅለ መንግሥት” ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት እነብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በ10 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ኾኑ

Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed wins the 2019 Nobel Peace Prize

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 11, 2019):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 (እ.ኤ.አ.) የዓለም ሰላም ኖቤል ሽልማት ዛሬ አሸነፉ። በዓለም ሰላም ለማሸነፍ እንዲበቁ ያደረጋቸው ከ20 ዓመታት በላይ ከኤርትራ ጋር የነበረውን ፍጥጫ በሰላምና በስምምነት እንዲቋጭ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ መሆኑ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢዜማ አነጋጋሪ መግለጫ አወጣ

Ethiopian Citizens for Social Justice Party (E-Zema)

ከተቋቋመ ጀምሮ የመጀመሪያ መግለጫው ነው

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 9, 2019):- የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ - ፍትሕ (ኢዜማ) በመባል የሚታወቀው ፓርቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የአገሪቱን ጉዳይ በተመለከተ “የኢትዮጵያ ሕዝብ የፍትሕና የነፃነት ጥያቄ በግዴለሽነት በሚንቀሳቀሱ ሰዎችና ተግባራቸው እንዳይታጠፍ ሁሉም ዘብ ሊቆም ይገባል” በማለት መግለጫ አውጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!