“ተልዕኮዬ ኢትዮጵያዊነትን ማስቀደም ነው” ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ለSBS ራዲዮ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Prof. Fikre Tolossa
ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ

አስውትራሊያ የሚገኘው የኤስ.ቢ.ኤስ ራዲዮ ከፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጋር ቃለምልልስ አድርጓል። በዚህ ቃለምልልስ ላይ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ በቅርቡ ለተደራሲያን ስላቀረቡት መጽሐፋቸው “የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” ጭብጥና ተልዕኮ ይናገራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ ሀብታሙ አያሌው የእስር ቤት ታሪኮች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Habtamu Ayalew
የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው

የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጋር የእስር ቤት ታሪካቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። "አንድ እስረኛ ተመርምሮ ሲመለስ መጀመሪያ የሚቀርብለት ጥያቄ ተሰቅለህ ነበር ወይም አልተሰቀልክም?" የሚል ነው - ከእስር የተለቀቁት አቶ ሀብታሙ አያሌው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሮፌሠር አለማየሁ ገብረማርያም ከአዲስ ድምፅ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Prof. Al Mariam

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (አለ ማርያም) ከጋዜጠኛ አበበ በለው ጋር በአዲስ ድምፅ ራዲዮ ቃለምልልስ አድርገዋል። ቃለምልልሱ ያተኮረው፣ የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግሥት ባለሥልጣናት አሜሪካን አገር ለሚገኝ ሎቢስት ወደ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በመክፈሉ ዙሪያ ላይ ሲሆን፤ በተለይም በአሜሪካ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ምን ማድረግ እንደሚጠበቅ ያብራራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

[ቃለምልልስ] ”ገጣሚ መባል ያስፈራኛል!” ወለላዬ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Welelaye's yerob gitem y2 n52ወለላዬ በየሳምንቱ ረቡዕ ረቡዕ በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ላይ ለሁለት ዓመታት ያህል ሳያቋርጥ 104 ግጥሞች በመጻፍ አስነብቦናል። በነዚህ ግጥሞቹ እኛን ሆኖ ውስጣችን ገብቶ ያልተናገርነውን ተናግሮልናል። ታዝበን ያለፍነውን ገልጾልናል። የሸሸግነው አጋልጦ አውጥቶብናል። የረሳነው አስታውሶ ወይ ጉድ አሰኝቶናል።

ግጥሞቹ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ አገራዊና ተፈጥሮዋዊ ነገሮችን ይዘው የሚያጠነጥኑ፤ ጭብጣቸው የተለያየ መልዕክት የሚያስተላልፍ በመሆኑ በአዲስ ረቡዕ አዲስ ነገር ለማንበብ በጉጉት ያስጠብቃሉ። ረቡዕ እንደሌላው ሁሉ ቀን ቢሆንም በወለላዬ ግጥም ምክንያት አንባቢዎቹ ዘንድ ደምቆ የሚታይ ሆኗል።

ደራሲና ገጣሚ አለማየሁ ታዬ ወለላዬ የአንድ ዓመቱን ረቡዕ ግጥም ሲያጠናቅቅ ስለ ግጥሞቹ አስተያየት ሲሰጥ፤ “የወለላዬ ግጥሞች አብዛኞቹ ባራት መስመር የተቋጠሩ እጥር ምጥን ያሉ የዘመናችን መዝሙሮች የየዕለት ሕይወታችን ሂሶች ናቸው። ግጥሞቹ ግልጽና ቀጥተኛ ስለሆኑ አደናጋሪነት አይታይባቸውም። የየስንኞቹን ሃሳብ ለመረዳትም ጥልቅ ምርምርና ተመላልሶ ማንበብን አይጠይቁም” በማለት ገልጾታል።

ኢትዮጵያ ዛሬም ይህን አስተያየት የምትጋራ ሲሆን፣ ወለላዬ በየሣምንቱ የሚያቀርበውን የረቡዕ ግጥም ሁለተኛ ዓመትን ከላይ በሰፈረችው ግጥም ስላጠናቀቀ ስለ ግጥም ሥራውና ስለ ገጣሚነቱ ምን ይላል ከሚለው ሃሳብ በመነሳት ጥያቄዎች አቅርበንለት ነበር። የሰጠንን መልስ እንዳለ አስፍረናል። መልካም ንባብ!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“በብሔረሰብ ከመደራጀት መላቀቅና ርዕዮተዓለማዊ ፍልስፍና ላይ በተመሠረተ ዕይታ መደራጀት አለብን” ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Dr. Fekadu Bekele”ቅኝ ገዥዎች ለመስፋፋት ሲሉ የብሔር ክፍፍልን በመጠቀም አገሮች እንዳይዳብሩ ያደርጉ ነበር። በእኛም አገር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብሔር ተኮር የፖለቲካ ኃይሎች ለውጥ ለማምጣት ቢሞከርም፤ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ይህ አልሠራም። ከብሔር ተኮር ይልቅ የአገሪቱ መሠረታዊ ችግሮች የእድገት፣ የሥልጣኔ፣ የሣይንስና ቴኮኖሎጂ፣ የማኅበራዊ ናቸውና ብሎ ቢንቀሳቀስ ኑሮ፤ ዛሬ የምናየው እጅግ አደገኛ ሁኔታ ላይ ባልወደቅን ነበር። በእነዚህ ላይ ቢተኮር ኑሮ እስካሁን ለውጥ ይመጣ ነበር።” ይላሉ ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ከኤስ.ቢ.ኤስ. ጋር ባደረጉት ቆይታ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”በኢትዮጵያ ያሉ ኦሮሞዎች የመገንጠል ሃሳብ የላቸውም” ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Prof. Fikre Tolossaፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ከአድራ ጋር ባደረጉት ክፍል ፪ ቃለምልልስ፤ ”ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኦሮሞዎች በጣም አርቀው የሚያስቡና፤ አገራቸው ኢትዮጵያ ብቻ እንደሆነች የሚያውቁ ናቸው። እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው አሁንም ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ተቻችለው፣ ተፋቅረው፣ በአንድነት የሚኖሩ ናቸው እንጂ፤ የሚለያዩ ወይንም የመገንጠል ሃሳብ ያላቸው አይደሉም” ሲሉ በኢትዮጵያ ስላሉ ኦሮሞች ይናገራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

[ሊያደምጡት የሚገባ!] ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ስለኦሮሞና አማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ ይናገራሉ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Yeoromo ena yeamara ewenetegna yezer menech by Prof Fikre Tolosa 01

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ "የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ" በሚለው አዲሱ መጽሐፋቸው ዙሪያ ከአድራ ጋር ጠለቅ ያለ ቃለምልልስ አድርገዋል። በዚህ ቃለምልልስ በተለይ የኦሮሞና የአማራን ዘር ከስር ከመሰረት ምንጩን ያብራራሉ። እውነት አማራ የገዥ መደብ ነበርን? ለሚለው የብዙዎች ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስደተኛው የኦሮሚያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁነዲን ሳዶ ይናገራሉ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Junedin Sado. አቶ ጁነዲን ሳዶ

የቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት የነብሩት ጁነዲን ሳዶ ከቪኦኤዋ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ቃለምልልስ አድርገዋል። አቶ ጁነዲን እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 11 ቀን 2012 ሀገር ጥለውና ኢህአዴግን ከድተው መሸሻቸው አይዘነጋም። አቶ ጁነዲን ከነበራቸው ከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ውስጥ የፌደራል መንግሥቱ የመገናኛ እና ትራንስፖርት ሚንስትር፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስትር እና የሲቪል ሰርቪስ ሚንስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታውሳል። ሙሉውን ቃለምልልስ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ!

“በታሪክ የአማራ ገዥ መደብ የሚባል ሥርዓት የለም” ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይርጋ አበበ

Prof Fikre Tolossa. ፕሮፌሠር ፍቅሬ ቶሎሳ

ፕሮፌሠር ፍቅሬ ቶሎሳ በቅርቡ “የኦሮሞ እና አማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” በሚል ርዕስ አንድ ታሪካዊ ዘውግ የተላበሰ መጽሐፍ አሳትመው ለንባብ አብቅተዋል። ፕሮፌሠር ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በኢትዮጵያ ጥንታዊና የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ስለ ኢትዮጵያ የቆየ የፌዴራሊዝም አስተዳደር ሥርዓት፤ ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ በስፋት ስለሚነገረው “የአማራ ገዥ መደብ” እና የኦሮምኛ ቋንቋ ለጽሁፍ የላቲን ፊደልን (ቁቤ) መጠቀሙን በተመለከተ እንዲሁም ስለ መጽሐፋቸው ይዘት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቃለ ምልልሳችንን ሙሉ ቃል ለአንባቢያን በሚመች መልኩ ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ “ስለ ኦሮሞና አማራ ትክክለኛ የዘር ምንጭ” ያብራራሉ!!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Prof. Fikre Tolossa ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ• ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች ነው
• አዳም የተፈጠረው ጎጃም፤ ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው
• ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አጥንቼ አለሁ ይላሉ …

ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ታዋቂው የሥነፅሁፍ ምሁር ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ፤ የፃፉት ”የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የተሰኘ አዲስ አነጋጋሪ የታሪክ መጽሐፍ ዛሬ (ቅዳሜ ሐምሌ 16 ቀን 2008 ዓ.ም.) ለገበያ ይቀርባል። የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ ማን እንደሆነ በጥናት ደርሼበታለሁ የሚሉት ፕሮፌሠሩ፤ እስከ ዛሬ የተለያዩ የታሪክ ምሁራን ከተናገሩት ፍፁም የተለየና አዲስ የጥናት ውጤት ማግኘታቸውን ይናገራሉ። የሁለቱ ቋንቋዎች አመጣጥም በጥናቱ ተካቷል ብለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ